“እፎይታ” በዚህ ሩጫ በበዛበት ዓለም ውስጥ የተመጋቢውን ጊዜ ሳትሻማ የነፍስን ረሃብ የምታስታግስ ጣፋጭ ሕብስት ናት። አንባቢ ለጥናት ሰፊ ጊዜ መመደብ ሳያስፈልገው በ 5 ደቂቃ ውስጥ ሊያጣጥማትና ተግባሩን እየከወነ በማሰላሰል ሊያመነዥጋት የሚችል ምጥን ጉርሻ ናት። በየዕለቱ የምትነበብ እንደመሆኗ መጠን ሳያሰልሱ የእግዚአብሔርን ቃል የማንበብና የማሰላሰል ብሎም የመተግበር ልማድ በአንባቢዎቿ ውስጥ ታዳብራለች። በውስጧ 60 የተለያዩ ተረኮችን ያዘለች እንደ መሆኗ ሳይታወቅ እየጣፈጠ እንደሚወርድ ምግብ ወደ ውስጥ ገብታ መድኃኒት የምትሆን በልክ የተሰነገች የጥሞና መድብል ናት።