የመጽሐፍ ቅዱስ የመላላክ ትምህርት
“በብዙ ምስክር ፊት ከእኔ የሰማኸውን ሌሎችን ለማስተማር ብቃት ላላቸው ለታመኑ ሰዎች
አደራ ስጥ፡፡” 2ጢሞ 2፡2
የእግዚአብሔርን ቃል ባሉበት ሥፍራ፣ በአጭር ጊዜና በአነስተኛ ወጪ
ይማሩና ይለወጡ!
በክርስትና ሕይወት ሥር ለመስደድና ለመታነፅ የእግዚአብሔርን ቃል መማር እጅግ ወሳኝ ነዉ፡፡ብዙዎች የእግዚአብሔር ቃል ለመማር ቢፈልጉም ወደ ትምህርት ቤት የመግባት ጊዜ በማጣት እና በቦታ ርቀት የተነሳ በምኞት ብቻ ተወስነዉ ይቀራሉ፡፡ እርስዎም ከእነዚህ አንዱ ከሆኑ የምሥራች እንንገርዎ፡፡ ጎልደን ኦይል አገልግሎት ጊዜዎትን በማይሻማ ሁኔታ በአነስተኛ ወጪ መሠረታዊ ትምህርቶችን በመላላክ ተምረዉ የአድቫንስድ ሰርተፍኬት ሊያገኙ የሚችሉበትን መርሃ-ግብር አዘጋጅቶ ይጠብቅዎታል፡፡
የምንሰጣቸው የትምህርት ዓይነቶች
- የመጽሐፍ ቅደስ አጠናንና አተረጓጎም ዘዴ
- የሮሜ መልዕክት ክፍል 1(በወንጌል የተገለጠ የእግዚአብሔር ፅድቅ)
- የሮሜ መልዕክት ክፍል 2(በወንጌል የተገለጠ የእግዚአብሔር ፅድቅ)
- የኤፌሶን መልዕክት ክፍል 1 (ርስትን ማወቅ)
- የኤፌሶን መልዕክት ክፍል 2
(በርስት መመላለስ እና ርስትን መጠበቅ) - እግዚአብሔርን የመምሰል ልምምድ
- የተራራው ትምሕርት
- የአዲስ ኪዲን ዲሰሳ
- የብሉይ ኪዲን ዲሰሳ
- ክርስቶስ፡- ማንነቱና የማዳን ሥራዉ
- ነገረ ፍፃሜ
ጠቃሚ መረጃዎች፡-
- የመላላክ ትምህርት እንደመሆኑ መጠን በማንኛዉም ጊዜ መመዝገብ እና መጀመር ይቻላል፡፡
- ትምህርቱ የሚሰጠዉ በአማርኛ ቋንቋ ነዉ፡፡
- ትምህርቱን በሚገባ የፈፀመ ተማሪ ከማዕከሉ የአድቫንስድ ሰርተፊኬት ያገኛል፡፡
- ትምህርቱን ለመጨረስ የሚፈጀዉ ጊዜ በተማሪዉ ፈጥኖ መጨረስ ላይ የሚመሠረት ሲሆን
- በትምህርቱ ሂደት ዉስጥ የሚፈጠሩ ጥያቄዎችን ኢትዮጵያ ውስጥ ከሆነ በፖ.ሳ.ቁ 18007
- በእያንዳንዱ ኮርስ እሽግ ዉስጥ የትምህርት መጽሐፍ፣ የፈተና ጥያቄዎች እና የመልስ መስጫ ወረቀቶች ይገኛለ፡፡ መጽሐፉን ጊዜ ወስደው በሚገባ ካጠኑ እና ፈተናዉን ከሠሩ በኋላ የመልስ መስጫ ወረቀቱን scan አድርገው ከቀጣዩ ኮርስ ክፍያ ጋር ቢልኩልን ቀጣዩን ኮርስ ወዲያውኑ እንዲደርስዎት እናደርጋለን፡፡
- በሚልኩልን የመልስ መስጫ ወረቀት ላይ ስምዎትን እና የኮርሱን ስም መሙላት አይዘንጉ፡፡
- የፈተና ጥያቄዎችን ከእርሶ ዉጭ ለማንኛዉም ሌላ ሰዉ ማስተላለፍ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
- ከመልሱ ጋር ስለ ኮርሱ ያለዎትን አስተያየት ጨምረዉ ቢልኩልን ደስተኞች ነን፡፡ ክፍያውን ለመፈፀም ኢትዮጵያ ውስጥ ከሆነ በባንክ ሂሳብ ቁጥራችን፣ የፖስታ ቤት ሐዋላን መጠቀም ወይም በግንባር አገልግሎቱ ቢሮ ድረስ በመምጣት ማከናወን ይቻላል፡፡ ከኢትዮጵያ ውጪ ከሆነ በቼክ Golden Oil Ministries U.S.A Inc. በሎ በመጻፍ (ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ) ወይም Bank of America Oklahoma Acc. #003040606351 ወይም በዚህ ድረ-ገጽ ላይ በሚገኘው መክፈያ በአስተማማኝ መንገድ መክፈል ይችላሉ። ለእርስዎ የሚያመችዎት ከሆነ የሁለንም ትምህርት ክፍያ በአንድ ጊዜ ማጠናቀቅ ጊዜ ይቆጥባል፡፡
ክፍያ
- ኢትዮጵያ ውስጥ መመዝገቢያ አንድ ጊዜ ብቻ የሚከፈል – 45 ብር
- ለአንድ ኮርስ – 115ብር
- የሰርተፊኬት እና ትራንስክሪፕት ማዘጋጃ- 20 ብር
- አጠቃላይ – 1330ብር
- ከኢትዮጵያ ውጪ መመዝገቢያ አንድ ጊዜ ብቻ የሚከፈል 25$
- ለአንድ ኮርስ 29$
- ለ 12 ኮርሶች አጠቃላይ 348$